አቡነ ተክለ ሃይማኖት

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማናቸው? አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታህሣሥ 24 ቀን በ1186 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ተወለዱ፡፡ አባታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ በሰባት ዓመታቸው ከግብፃዊው አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለክህነት መጠራት በዚህ ዓለም ትዳር መሥርቶ፣ የዓለሙንም ሥራ ሠርቶ መኖር አያስፈልግም ከሚል ፍልስፍና የመነጨ አይደለም፡፡ ከ8ኛው መክዘ ጀምሮ በሀገሪቱ የመንፈስ መቀዛቀዝ ይስተዋል ነበር፡፡ ዮዲት ጉዲት መንግሥቱን ይዛ በክርስትናው ላይ ከዘመተች በኋላ ሰሜኑ እና ደቡቡ ተቆራርጧል፡፡ የሃሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ኢትዮጵያዊ ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ ነው የተክለ ሃይማኖት የጥሪ ምክንያት፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ዕረፍት በኋላ ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው ለወንጌል ስብከት ወጡ፡፡ የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከመሄዳቸው በፊት ቅስናን ተቀብለው በሸዋ እና በዳሞት ማገልገላቸውን ይገልጣል፡፡

Read more: አቡነ ተክለ ሃይማኖት

ታህሣሥ ፲፱

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሳች

 

 ቤተክርስቲያናችን ዓመታዊ ሆነ ወርሃዊ በዓላትን ስታከብር ካለ ምክንያት አይደለም፡፡ በመሆኑም የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለምን   እንደምናከብር ከዚህ እንደሚከተለው በጥቂቱ እንማማራለን፡፡ እግዚአብሔር ይጨመርበት፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ   ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ እጅጉን ተፈሪ እና ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ በስዕለት ሰሚነቱ፣ ብሥራት አብሣሪነቱም የሚመሰገን መልአክ ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንም የቅዱሳን መላእክት ወርኃዊ በዓላቸውን በጸሎት እና በምስጋና የምታከብር በመሆኗ ታህሣሥ ፲፱ ቀን የብርሃናዊው መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሠለስቱ ደቂቅን ከዕቶነ እሳት (ከነደደ እሳት) ማዳኑን ምክንያት በማድረግ ታከብራለች፡፡

 

Read more: ታህሣሥ ፲፱

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine