ሆሣዕና

ወደ ደብረዘይት ሲደርስ ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ከፊታችሁ ወዳለ ሀገር ሂዱ ሰው ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጭላ ታገኛላችሁ፣ ፈትታቸሁ አምጡልኝ ለምን ትፈታላችሁ የሚል ቢኖር ጌታው ይፈልገዋል በሉ ብሎ ላካቸው፡፡ ሔደው ጌታው ይፈልገዋል ብለው ፈትተው አመጡለት ልብሳቸውን ጎዝጉዘውለት በዚያ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሰማይ ተከፍቶ ፀሐይ ከአህያው ፊት ሁና ስትሰግድ ምድሪቱም ብርህት ስትሆን መላእክትም ከሰማይ ወርደው አህያውን ከበው ሲያመሰግኑት አይተው ልብሳቸውን ከመሬት እያነጠፉ ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር  በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተመሰገነ ነው እያሉ አመስግነውታል፡፡

ኢየሩሳለሌም ሲደርስ ከገጹ ብርሃን የተነሣ ከተማዋ ብርህት ሆነች፡፡ ሕዝቡ የሆነውን ሊያዩ ወጡ፡፡ ሕፃናት ፀሐይ ስትሰግድለት መላእክት ከበው ሲያመሰግኑት አይተው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የሰሌን ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል፡፡ ሆሣዕና ማለት በልዕልና ጸንቶ የሚኖር መድኃኒት ማለት ነው፡፡

ሕፃናቱ ሦስት እልፍ ናቸው፡፡ የነርሱ ምሥጋና ከመላሰእክት ምስጋና ተዋህዶ ኢየሩሳሌም ተናወጸች፡፡ ረበናተ አይሁድ ምን መጣብን ብለው ደንግተው ቢወጡ ሕፃናቱን ሲያመሰግኑ አገኙ፡፡ እግዚአብሔር በሚመሰገንበት ምስጋና የዩሴፍን ልጅ እንድታመሰግኑ ማን አስተማራችሁ?  አሏቸው፡፡ እናንተ እውሮች ፀሐይ ስትሰግድለት መላእክት ሲያመሰግኑት አታዩምን? መዝ 8፡3 ያለው አላነበባችሁም? አሏቸው፡፡  ማስተው /መቆም/  የማይቻለቸው ቢሆን ሄደው ጌታን ዝም እዲሉ ሕፃናቱን እዘዛቸው አሉት፡፡ እኒህ ሕፃናት ዝም ቢሉ ደንጊያዎች አያመሰግኑኘ መሰላችሁ? አላቸው ወዲያው ድንጋዮች ከደብረዘይት እየዘለሉ መጥተው በስመ እግዚአብሔር ብለው አመስግነውታል፡፡ መቅደሱን ሦስት ጊዜ ዞሮ በጅራፍ እየገረፈ አስወጥቷቸዋል፡፡ ሜቴ 21፡10

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine