ዘመነ ጰራቅሊጦስ

በበዓለ ሠዊት ካህናተ ኦሪት ዓሥራቱን' በኩራቱን' ቀዳምያቱን ይቀበሉበት ነበርና ይህ በዓል በዘመነ ኦሪት በዓለ ሠዊት ይባል ነበር፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለውበታልና ከዘመነ ሐዋርያት ወዲህ በበዓለ ሠዊት በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡ ከዚሁ ዘመን በኋላም ተያይዘው ጾመ አስቴር' ጾመ ዮዲት የሚባሉ አጽዋማት ነበሩአቸው፤ በጾመ አስቴር የእስራኤል ምክረ ሞት ተፈጽሞበት ነበር፡፡ ኋላም ረቡዕ የጌታ ምክረ ሞት ተፈጽሞበታልና በዘመነ ሐዲስ ጾመ ረቡዕ ገብቶበታል፡፡ በጾመ ዮዲትም እንዲሁ ሆለሆርኒስ ድል ተደርጎበታል፡፡ በዘመነ ሐዲስናም በዕለተ ዓርብ ዲያብሎስ ድል ሆኗልና በጾመ ዮዲት ጾመ ዓርብ ገብቶበታል፡፡

ዘመነ ጰራቅሊጦስ የሚባለው ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ ከሃምሳኛው ቀን ጀምሮ ቀጥሎ እስከ አለው እሑድ ድረስ ያለው 8 ቀን ነው በዚህም መሠረት ከትንሣኤ እስከ ጰራቅሊጦስ /እስከ ወረደ መንፈስ ቅዱስ/ 58 ቀን ይሆናል፡፡ . . .

Read more: ዘመነ ጰራቅሊጦስ

መጋቢት 27 ስቅለት

ሥጋውን በኅብስት ደሙን በወይን አስታኩቶ ተቀብሎ ሲያቀብላቸው የስምዖን ዘለምጽ ሚስት ዶሮ አሰናድታ አቀረበችለት፡፡ የተናገረው ሊፈጸምግድ ነውና ኅብስቱን ቆርሶ ከወጡ ጠቅሶ ለይሁዳ ሰጠው፡፡ ሰይጣን ከኅብስቱ ጋር ተዋህደው ልቡ በቅናት ነደደ፡፡ ሥጋው ደሙ ሰይጣን ያርቃል እንጂ አያቀርብም ነበር፡፡ ዳሩ ግን ዕዳ ፍዳ የሚቀበልበት ነውና ሳይበቁ የሚቀበሉ ዕዳ እንደሚሆንባቸው ለማጠየቅ ነው፡፡ ሂድ ያሰብከውን ፈጽም አለው፡፡ ወጥቶ ሄደ፡፡ ይሁዳ እንደወጣ ጌታ ዶሮውን በቃሉ ተናግሮ በእጁ ዳሶ ሕያው ከአደረገው በኋላ ይሁዳ ተከትለህ የሚያደርገውን አይተህ የሚናገረውን ሰምተህ ለደቀመዛሙርቴ ንገራቸው አለው፡፡ እየበረረ ወጥቶ ተከተለው፡፡ ከቤቱ ገብቶ ከሚስቱ ተኝቶ በዋጋ አሳልፎ ሲሰጠው መከረ፡፡ ሔዶም አይሁድን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሠጡኛላሁ? አላቸው፡፡ ስሞ ሲያሳያቸው ተስማምተው ሠላሳ ብር ሰጡት፡፡ የተነገረበት ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ምን ተብሎ ተነግሯል ቢሉ ነቢዩ ዕንባቆም ለማስተማር ሲሔድ የይሁዳ አባት ከባልንጀሮቹ ጋር ከድንጋይ ላይ ተቀምጦ ባልንጀሮቹ ሲነሱለት እርሱ ተቀምጦ አሳለፈው፡፡ ሲያስተምር ውሎ ሲመለስ ከዚያው ተቀምጦ አገኘው፡፡ እንዳይነሳ ኮርቶ እንዳይቀመጥ ፈርቶ ተሸፋፍኖ አሳለፈው፡፡ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል ከዚህም ሰው የሚወለደው አባቱን የሚሰልብ እናቱን የሚያገባ መምህሩን የሚሸጥ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናግሮበታል፡፡ ከቤቱ ገብቶ ለሚስቱ በግድ ካልተነሳህልኝ ብሎ እንዲህ አለኝ ብሎ ነገራት እሷም ደግ ያደረግህ መሰለህ? ታላቅ ሰው ሲመጣ ተቀምጦ ማየት ይገባልን?  ብላ ገሠጸችው፡፡ ከዚህ በኋላ መገናኘቱን አንተው ብለው መክረው ሲጨርሱ አንድ ቀን ፈቃደ ሥጋ አሸንፎት ተገናኛት፡፡ ይሁዳ ተጸነሰ፡፡ በተወለደ ጊዜ በሳጥን አድርገው ከባሕር ጣሉት፡፡ ስምዖን አግኝቶ አሳደረው፡፡

ተያያዥ ገጾች

ጥቅስ

‹‹ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ›› ( ሲራክ 5፡7)

‹‹ፈጥነህ ስማ፤ ቃልን ለመመለስ ግን የታገስክ ሁን›› (ሲራክ 5፡11)

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም›› (ሲራክ 2፡15)

Joomla templates by Joomlashine